የሰው ልጅ ዐይን በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ባሉ የጤና ችግሮች ምክንያት ሊጎዳ የሚችልበት ሰፊ አጋጣሚዎች አሉ ።
እንደ ስኳር ፤ ደም ግፊት ፤ ኩፍኝ እንዲሁም ሌሎች በክትባት በቀላሉ ሊወገዱ የሚችሉ ህመሞች ተገቢው ክትትል ሳይደረግ ስር በሰደዱ ጊዜ የአይናችንን ብርሀን ከመቀነስ አልፎ እስከማጥፋት ይደርሳሉ ።
ከነዚህ ህመሞች በተጨማሪ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ከቴክኖሎጂ ጋር እየተሳሰረ ከሞባይል እና ከኮምፒውተር ጋር ያለን ቁርኝት እየጨመረ በመሄዱ በዚህ ሳቢያ የሚከሰት የዐይን ህመም በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በዚህ ጉዳይ ላይ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ኦፕቶሜትሪስት ስንሻው ሹምዬ አንድ ሰው በቀን በስክሪን ላይ ለምን ያህል ሰዓት መቆየት አለበት ለሚለው ሙያዊ ምላሽ ሰጥተውናል።
ወጣቶች ስክሪን ላይ የሚያጠፉት ጊዜ በፈጠረባቸው ህመም በተደጋጋሚ ወደ ህክምና እይደሚመጡ የነገሩን ኦፕቶሜትሪስት ስንሻው በአስገዳጅ ምክንያት በስክሪኖች ላይ መቆየት ካለብንም መውሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች እንዳሉ ጠቁመውናል።
መነጽሮችንም ቢሆን ያለሀኪም ትዕዛዝ መጠቀም አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመውናል።
ስክሪን ላይ ሰፊ ጊዜ ባለማሳለፍ የህክምና ባለሞያ ምክሮችን በመተግበር እንዲሁም በ ዓመት 2 ጊዜ ምርመራ በማድረግ የዓይናችንን ጤንነት መጠበቅ እንደሚገባንም ገልጸዋል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-10-31
