በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ለተጨማሪ ቀናት መራዘሙን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጭ ለቢቢሲ ገለጹ።
ቢቢሲ ያናገራቸውና ድርድሩን በቅረበት የሚከታተሉት ምንጭ በሁለቱ ወገኖች መካከል አስካሁን በተደረገው ንግግር የተነሱ ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
ነገር ግን በመካሄድ ላይ ያለው ድርድር ረቡዕ ዕለት የሚጠናቀቅ ከሆነ፣ ስለተካሄደው ንግግር ሂደት እና ውጤቱ የጋራ መግለጫ እንደሚወጣ ዲፕሎማቱ ገልጸዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-10-31
