ሀገሬ ቲቪ

በሰሜኑ ጦርነት የወደመው የመካከለኛ ኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ስራ ተጠናቀቀ

በሰሜኑ ጦርነት የወደመው ከአላማጣ እስከ ቆቦ ያለው የኤሌክትሪክ መስመር የጥገና ስራ መጠናቀቁ ተገለጸ።

በአካባቢው የሚከናወነው የመካከለኛ ኤሌክትሪክ መስመር ጥገናው የተጠናቀቀው ሙሉ በሙሉ ስለመሆኑ የወልዲያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ወልደ ሰማያት ገልጸዋል።

አቶ ሽመልስ ከአላማጣ እስከ ቆቦ ያለውን አካባቢ እንደገና የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከአላማጣ እስከ ላሊበላ ያለው የትራንስሚሽን መስመር የጥገና ስራም 90 በመቶ ተጠናቋል ተብሏል።

የአካባቢውን የመካከለኛ መስመር ጥገና በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-31