የቀድሞ የብራዚል ፕሬዝዳንት የነበሩት ልዊስ ኢናሽዮ ሉላ ዳ ሲልቫ በአሁኑ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫም አሸናፊ ሆኑ።
ሉላ ተፎካካሪያቸውን ጄር ቦልሶናሮን 50 ነጥብ 8 በመቶ ለ 49 ነጥብ 2 በመቶ በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፈዋል።
ፕሬዝዳንትነቱን ከ11 ዓመታት በኋላ ሉላ በድጋሜ ያገኙበት ምርጫው ለሁለተኛ ዙር በተካሄደ የብራዚል የምርጫ ታሪክ የውጤት ልዩነቱ ትንሹ ነው ተብሎለታል።
ሉላ የማህበራዊ ጉዳዮች ላይ፣ ዝቅተኛ ደመወዝ መጨመር እና የመንግስት ተቋማትን አቅም ማጠንከር ላይ ፣ ድህነትን እና ረሃብን ለመቀነስ ብሎም የአማዞን ጥብቅ ደን ውድመትን ለመከላከል እንደሚሰሩ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው አስታውቀዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-10-31
