ሀገሬ ቲቪ

የሰላም ንግግሩን ከባድ የውጪ ጣልቃ ገብነት አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል ተባለ

በደቡብ አፍሪካ እየተካሔደ ባለው የሰላም ንግግር በርካታ የውጪ ጣልቃገብነት እንዳለ ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ኢትዮጵያውያኖች የራሳችንን ችግር መፍታት እንደምንችል መረዳት አለብን ሲሉ ተናገርዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲጂቲኤን ለተባለው የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው ይህን የተናገሩ።

የህወሓት ቡድን የሀገሪቱን ሕግ እና ሕገ መንግሥት እንዲያከብር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ ክልል እንዲንቀሳቀስ ለማሳመን እየሞከርን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

ፍላጎታችችን መረዳትና በሕገመንግሥቱ ማመን እንዲሁም ከተመሩ የታለመው ሰላም ይሳካል ብዬ አስባለሁ ሲሉም ተናግረዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-01