ሀገሬ ቲቪ

ለሱስ የማጋለጥ ባሕሪ ያለው መድኃኒት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ ነው

የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የትራማዶል መድኃኒት ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር አደርጋለሁ አለ።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከጤና ባለሙያ ትዕዛዝ ውጭ በርካታ ወጣቶች ለህመም ማስታገሻ በሚል አለአገባብ እየተጠቀሙ እንደኾነ መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል።

መድኃኒቱ በመደጋገም መውሰድ ከበድ ያለ ሱስ የማሲያዝ አቅም ያለው ነው።ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲሁም መድኃኒቱ ለሕክምናው አስፈላጊ በመኾኑ ከዚህ በኋላ መድኃኒቱ በከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚሸጥ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-01