ሀገሬ ቲቪ

ከዩክሬን ወደብ ስንዴ እንዲጓጓዝ ከተደረሰው ስምምነት ሩሲያ ራሷን አገለለች

በተባበሩት መንግሥታት አሸማጋይነት ከዩክሬን እህል ይዘው የሚወጡ መርከቦች በጥቁር ባሕር ያለአንዳች የደኀንነት ሥጋት ማለፍ እንዲችሉ ከፈረምኩት ስምምነት ለጊዜው ራሴን እንዳገለልኩ ዕወቁልኝ ብላለች ሩስያ።

ዩክሬን በሰውአልባ አውሮፕላን የጦር መርከቦቼን ላይ ጥቃት ስላደረሰች ስምምነቱን ለመቀልበስ እገደዳለሁ ስትል ሩሲያ አስታውቃለች።

የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ ጥቃቱ ደረሰ በተባለበት ዕለት ምንም ዓይነት መርከብ በጥቁር ባሕር ኮሪደር አልነበርም ሲል የሩሲያን ክስ አስተባብሏል።

ሰኞ ዕለት እህል የጫኑ 12 መርከቦች ከዩክሬን ወደብ የተነሱ ሲኾን 40 ሺህ ቶን ስንዴ የጫነችው መርከብ መዳረሻዋ ኢትዮጵያ ነበር ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-01