ሀገሬ ቲቪ

በብራዚል ምርጫ ሉላ ዳሲልቫ አሸናፊ ሆኑ

የላቲን አሜርካዋ ሃገር በዳንስ እና በጭፈራ ተናጠች ። የተለመደው ካርኒቫል ይመሰላል በርካታ ዜጎች በአደባባይ ደስታቸውን ገለጹ ።

18 ወራትን በ እስር ቤት የማቀቁት ሊውዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን አሸንፉ። ግራ ዘመም የፖሊካ ስርዓት ዳግም ወደ ብራዚል መልህቁን ጣለ ።

እጅግ መከፋፈል ከታየበት የሁለቱ ተቀናቃኞች የምርጫ ሉላ 50.9 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸንፋቸው ታወጀ።

የብራዚል መንግሥት የነዳጃ ኩባንያ የሆነው ፔትሮ ብራስ ጋር ለመሰራት ስምምነት እና እና ጉቦን ተቀበልዋለ በማለት ለ 18 ወር ጥፋትኛ ናቸው በሚል ተወስኖባቸው ዘብጥያ ወርደው ነበር ።

የ2018ቱ ምርጫ እንዲይሳተፉም በቀኝ ዘመሙ ፓርቲ ጄር ቦልሶናሮ ቁማር ተቆምሮባቸዋል ። ብራዚልን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የነበሩት ቦልሶናሮ በብዙ መልኩ ይተቹ ነበር ።

በኮቪድ 19 ከ 680 ሺ በላይ ዜጎች እንዲያልቁ እና የጥንቃቄ መንገዶች ላይ በሚያስዩት ቸለትኘነት ይተቹም ነበር ።

ብራዚልን ከ 2003 እስከ 2010 የመሩት የሁን ፕሬዝዳንትም ቢሆኑ በማህበራዊ ጉዳዮች አና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ማሻሻያ ቢያደርጉም እሳቸውም ቢሆን በአየር ንብረት ለውጥ እና በ አምዞን ድንን በመጠበቅ ላይ ትኩረት ባልመስጠታቸው ይተቻሉ ።

ሉላ በራዚል በ 2014 እና 2016 ባዘጋጀቻቸው አለማቀፍ የስፖርት ወድድሮች ቁልፍ ሚናን ተጫውተዋል ። የቀድሞ የአሜሪካ ፕርዚዳን ባራክ ኦባማም ቢሆኑ እንዲ ይሏቸዋል “የምድራች እጅግ ታዋቂ የፖለቲካ ሰው” ።

ይህችን ሀገር ማስተካከል ያስፈልገናል... ስለዚህ የብራዚል ሕዝብ እንደገና ፈገግ ማለት ይገባል የሚሉት ሉላ ፓርቲያቸው ከዚህ በኋላ ሰፊ ሰራ ይጠበቀበታል ።

የሰራ አጥነት ፣ ፍትሃዊ የሀብት ከፍፍል ፣ የአየር ንብረት ለወጥ ፣ ድህነት እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ የብራዚል ራስ መታት ነው ። በምርጫው ተሸንፉት የቦንሶናሮ ደጋፊዎች በአደባባይ መመገኘት ሃዘናቸውን ሲገልጹ አምሽትዋል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-01