ግዙፉ የቻይና የኦን ላይን የመገበያያ ስርዓት አሊባባ በኢትዮጵያ ሊጀምር ነው።ዛሬ ይህንን የመገበያያ ስርዓት ለማስጀመር ይረዳል የተባለ ሰነድ በኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲውት፣ በአሊባባ ቢዝነስ ግሩፕ አጋር ዌል ክላውድ እና በከሃሊ የስትራቴጂክ አማካሪ አገልግሎት ድርጅት መካከል ተፈርሟል።
ስምምነቱ ግዙፉን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት መገበያያ ቴክኖሎጂ በማቅረብ የሚታወቀውን የአሊባባ የኢ-ኮሜርስ ሥርዓት በኢትዮጵያ ለማስጀመር ያለመ ነው።
በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለስርዓቱ አስፈላጊ የሆነውን የዳታ ቋት እና ሌሎች ደህንነታቸው የተጠበቁ መሠረተ ልማቶችን እንደሚያቀርብ በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
መረጃውን ኢንስቲትዩቱ የማህበራዊ ገፅ አግኝተነዋል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-11-01
