
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ልዩ ፍርድቤት ከአራት ዓመት በፊት በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ በተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች ላይ ተሳታፊ ነበሩ ባላቸው ሶስት የሚሊሺ አባላት ላይ የመጀመሪያውን እና ታሪካዊ ነው የተባለውን ፍርድ ሰጥቷል።
ልዩ ፍርድ ቤቱ 1996ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱ የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን መርምሮ ውሳኔ እንዲሰጥ የተቋቋመ ነው። ሰኞ እለት የመጀመሪያ የፍርድ ውስኔ መስጠቱ ነው ታሪካዊ ያስባለው።
በዚህም መሠረት ሁለቱ ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች በ 20 ዐመት እሥራት እና አንደኛው ተከሳሽ በዕድሜልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍ/ቤቱ ወስኗል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-01