የተባበሩት መንግስታት የአለም ሜትሮሎጂ ድርጅት (WMO) እና የአውሮፓ የአየር ንብረት ለውጥ አገልግሎት ኮፐርኒከስ አዲስ ባወጡት ሪፖርት መሰረት አውሮፓ ከየትኛውም የአለም ከፍል በተለየ በከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር እየተናጠች ነው ብለዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ሲነሳ ሁሌም የችግሩ ገፈት ቀማሾች ዳሃዎች የአፍሪካን እስያ ሃገራት እንጂ የምራባውያን ጣጣ እንዳልሆነ ነበር የሚገልጸው ።
ለዚህም ነበር ለአየር ንብረት ብክለቱ ያበረከታችሁትን ያክል ነገሩን መሰመር ለማስያዝም አግዙ ይሚለው ድምጽ በየዓለም አቀፍ መድረኩ ከፍ ብሎ ሲሰማ የነበረው።
አሁን ግን ጉዳዩ የነሱም እንደሆነ በትሩም እነርሱ ላይ ማረፍ መጀመሩን የሚይሳዩ ሪፖርቶች እየወጡ ነው።
አውሮፓ በማይታመን መልኩ በፈጣን ሙቀት መጨመር እየተመታች ነው ከፈረንጆቹ 1991-2021ባሉት ጊዜያት ውስጥ ብቻ የአልፓይን ግግር በረዶዎች በአማካይ 30 ሜትር ድረስ ቀልጠዋል።
የተባበሩት መንግስታት የአለም ሜትሮሎጂ ድርጅት እንደሚለው በየ10 አመቱ በአማካኝ 0.5 ዲገሪ ሴንቲግሬድ የሙቀት መጠን ጭማሪ በአውሮፓ ታይቷል።
በተባበሩት መንግስታት የአለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ቃል አቀባይ ክሊር ኑልስ እንዳሉት የአርክቲክ ግግር በረዶ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየቀለጠ ይገኛል ይህ ደግሞ ለአውሮፖ የሙቀት መጨመር ማሳያና የጉዳዩ ክብደትን አመላክች የማስጠንቀቂያ ደውል ነው ብለዋል፡፡
በአውሮፓ በከፍተኛ የአየር ሙቅት መጨር ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በቀጥታ ችግር ውስጥ እንዲወድቁ ሆነዋል።
ከ50 ቢልዮን ዩሮ በላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳትም አስከትለዋል። ከእነዚህ መካከል 84 በመቶ የሚሆኑት ጎርፍ ወይም አውሎ ነፋስ ምክኒያት የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል።
ለወትሮው ውሃ እንደልብ ይንፎሎፎልባቸው የነበሩ ወንዞችም ደርቀው ባዶ ሜዳም ሆነው የታዩባቸው የአውሮፓ ሀገራት አሉ።
በተባበሩት መንግስታት የአለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ፔተሪ ታላስ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ አውሮፓ "የምድር ሙቀት መጨመርን የሚያሳይ ገጽታ ያላት አህጉር ከመሆኗም በላይ ህዝቦቿም ከአስክፊው የአየር ሙቀት ፀባይ እና ከሚያስከትለው መዘዝ ጋር አብረው ለመኖር እንደሚገደዱ ተናግረዋል።
በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸውን በመቀነስ ረገድ በጣም ጥሩ ስራ እየሰሩቢሆንም ለችግሩን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የአለም ሙቀት መጨርን ለመግታት እየተስራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መገለጹን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
በማህሌት አማረ
2022-11-03
