ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ''የሌማት ትሩፋት'' የተሰኘ ሀገር አቀፍ የወተት፣ዶሮና ማር ልማት መርሃ-ግብር አስጀመሩ።
መርሃ-ግብሩ ለቀጣይ 4 አመታት የሚተገበር ሲሆን፣ ዋና ግቡም የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እና የምግብ ስርዓትን ማሻሻል ነው።
በዚህም የወተት ምርትን 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ሊትር አመታዊ ምርት ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር ከፍ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል።
የዶሮ ስጋ ምርትን ደግሞ ከ90 ሺህ ቶን ወደ 240 ሺህ ቶን ለማደረስ እቅድ መያዙ ተመላክቷል።
በብሩክ ያሬድ
2022-11-03
