ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው የሞባይል ኔትዎርክ መሥራት መጀመሩን ኢትዮቴሌኮም አስታውቋል።
እነዚህ አካባቢዎች በሰሜኑ የሀገሪቱ ጦርነት ምክንያት የኔትዎርክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው ነበር።
ጄኔሬተር ነዳጅ ወደ አካባቢው በመላክ አላማጣ እና ኮረም ሙሉ ለሙሉ የኔትዎርክ አገልግሎት እንደሚያገኙ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጽሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ሥራ አስፈጻሚዋ አክለው በቆቦ፣ ሮቢት፣ ዞብል፣ ጎቢዬና ዋጃ የመልሶ ጥገና ተከናውኖ የቴሌኮምአገልግሎት ጀምሯል ብለዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-03
