
በ2025 ያላትን የነዳጅ ሃብት ለገበያ ለማቅረብ ያቀደችው ዩጋንዳ ዕቅዶ እንዲሳካ ቻይና የገንዘብ ድጋፍ እንድታደርግላት ጠየቀች።
ከጎረቤት ሃገር ታንዛኒያ ጋር በመሆን የነዳጅ ምርቷን ለማቅረብ ይረዳት ዘንድ ለምትዘረጋው የነዳጅ ቱቦ መስመር ዝርጋታ የሚውል ገንዘብ ነው ከቻይና የጠየቀችው።
የዩጋንዳ ማእድን እና ኢነርጂ ሚኒስተር ሩዝ ናካብሪዋ ለመጀመሪያ ጊዜ እርግጠኛ ሆነው ሀገራቸው በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2025 ነዳጅ አምርታ ለገበያ እንደምታቀርብ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱን ከዩጋንዳ ጋር በጋራ እየሰራች ያለችው ታንዛኒያ ፐሬዝዳንት ሲማ ሱሉል የገንዘብ ድጋፍ ከቻይና በእርግጠኝነት የሚገኝ ቢሆንም አሜሪክና አውሮፓ ለጵሮጀክቱ ድጋፋቸውን ቢያደርጉ የበለጠ እንደሚሹ ተናግረዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-11-03