ሀገሬ ቲቪ

ሰሜን ኮርያ በአንድ ቀን ከደርዘን በላይ ሚሳየሎችን አስውነጨፈች

ሰሜን ኮርያ ከ12 በላይ የአጭርና እረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በአንድ ቀን አስውንጭፋለች።

ሁሉም ያረፉት ባህር ላይ መሆኑ ቢገለጽም በአካባቢው ያለውን ውጥረት አባብሶታል።

በተለይ ደቡብ ኮርያ ሚሳየል በማስውንጨፍ ምላሽ መስጠቷ ነገሩን ይበልጥ እንዳካረረው ነው የተገለጸው ።

ጃፓንና ደቡብ ኮርያ እንደጠብ አጫሪ የሚቆጥሯት ሰሜን ኮርያ አሚሪካና ደቡብ ኮርያ በጥምር የሚያደርጉትን የጦር ልምምድ ካላቆሙ እርሷም ሚሳየል ማስውንጨፏን እንደማታቆም አስታውቃለች ።

በብሩክ ያሬድ
2022-11-03