ሀገሬ ቲቪ

በመተንፈሻ መሳሪያ በመታገዝ ማራቶን የሚሮጠው ሰው

ብዙዎች የጥንካሬ ተምሳሌት ይሉታል የሰው ልጅ እችላለሁ ብሎ የማያስበውን በማድረጉ በመገናኛ ብዙሀን ከብዙዎች አድናቆት ተችሮታል ።

ይህ ሰው ራሲል ዊንውድ ይባላል በመተንፈሻ አካላቱ ላይ ከፍተኛ ችግር አለበት የሳንባው የመስራት አቅም 30 በመቶ ብቻ እንደሆነ ከሀኪሞች ተነግሮታል ነገር ግን የማራቶን ሯጭ ነው።

እንዴት ተደርጎ የብዙዎች ጥያቄ ነው ራስል ግን እንደቀልድ የሚከውነው ተግባር ሆኗል። ራስል በ36 ዐመቱ በአንጎሉ ውስጥ የደም መፍሰስ አደጋ ያጋጥመዋል ።

በወቅቱም አልኮል መጠጣት እና ማጨስ በፍጥነት አቁሞ ስፖርት መስራት እንዳለበት ከሀኪሞች ይነገረዋል ።

ራስልም የተባለውን በማቆም ሩጫ መሮጥ ጀመረ ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን በፊት ያደርጋቸው የነበሩ አላስፈላጊ ተግባራት በፈጠሩት ጫና የመተንፈሻ አካላቱ ተዳክሞ ያለ ኦክስጅን መንቀሳቀስ አቃተው ።

ይህ ሰው ተስፋ አልቆረጠም የተፈጠረብኝ ችግር ስፖርት ከመስራት አያግደኝም በማለት ለመተንፈስ የሚረዳውን መሳሪያ አፊንጫው ላይ አርጎ ሩጫውን ቀጠለ ። ያውም ማራቶን ።

ማራቶን መሮጥ እንኳን ሳንባው ተዳክሞ 30 በመቶ ለሚሰራ ሰው ይቅርና ሙሉ ጤነኛ ለሆነ ነው ሰው እጅግ ፈታኝ ነው ።

ሳንባዬ መዳከሙን በሰማው ጊዜ ልቤ በእጅጉ አዘነ የሚለው ራስል ጤንነቴን በስፖርት መጠበቅ እንዳለብኝ ባምንም ከሀኪሞች የታዘዘልኝን መድሀኒት እና ክትትል ግን አላቆምኩም በሁሉቱም ህመሜን እየተጋፈጥኩት እገኛለው ብሏል።

በራስል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች የማይንቀሳቀሱ ፤ መጠነኛ የ እግር ጉዙ የሚያደርጉ ወይም ደግሞ አልጋ ላይ የተኙ ናቸው ።

ራስል ግን የማቻለውን በማድረግ ለብዙዎች ምሳሌ ሆኗል ። አሁን ላይ 56ኛ ዓመቱን የያዘው ራስል በቅርቡ የተካሄደውን 26.2 ኪሎ ሜትር የሚርቀውን የችካጎ ማራቶን በ6 ሰዓት፣ ከ28 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ በሆነ ሰዐት ማጠናቀቅ ችሏል።

ታዲያ በኦክሲጂን መሮጥ አጃይብ አያሰኝም?

በዮሴፍ ከበደ
2022-11-03