ሀገሬ ቲቪ

አጼ ምንሊክ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው የነገሱበት ቀን

የኢትዮዮጵያ ከብዙ ዘመናዊ ጉድዮች ጋር እንድትተዋወቅ በማድረጋቸው ይታወቃሉ መኪና ስልክ ወፍጮ ከነዚህ ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ነጭን ያሸነፈ ብቸኛም መሪ ናቸው አጼ ምኒልክ። በዘመናዊቷ ኢትዮጲያ ወስጥም ዛሬም ደረስ ይታወሳሉ ።አጼ ምንሊክ በኢትዮጲያ የንግሰና ቆብን የደፉት በዛሬው ቀን ከ 133 አመት በፊት ነበር ።

ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ነሐሴ 12 ቀን 1844 ዓ.ም. ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወለዱ።

ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሃፋቸው ሰለ ምንሊክ ሰም አሰያየም እንዲ ይላሉ አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጁን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለው ስም አወጡ።

እሳቸው “…ምኒልክ በሚል ስም የሚነግሥ ንጉሥ ኢትዮጵያን ታላቅ ያደርጋታል” የሚል ትንቢት ስለነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለው ነበር።

ሆኖም፣ በህልማቸው ከልጁ ጋር አብረው ቆመው ከሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፤ በእግር የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸው ከረገጡት ልጁ የረገጠው ረዝሞ አዩ። ከዚህ በኋላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም። የሱ ነው። ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለው አዘዙ ይላል መጽሐፉ ።

አፄ ተዎድሮስ ወደ ሸዋ ለግዛት ማስገበር በገቡ ጊዜ ምኒልክ ገና የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበሩ ፤ የድፍን አማራንና የወሎን ጦር አስከትተው የሸዋውን ንጉሥ ኃይለ መለኮትን ለማስገበር ሸዋ ገቡ።

ሁለቱ መሪዎች ጦርነት ለመግጠም ተዘጋችተው ሲጠባበቁ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ባደረባቸው ሕመም አረፉ። በዚህ ጊዜ የሸዋ መኳንንት ሕጻኑን ምኒልክን ከጠላት እጅ እንዳይወድቅባቸው ይዘው ሸሹ፤ የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት በረከት ላይ ገጥሞ የምኒልክ ሹማምንት እነአቶ በዛብህ፣ እነአቶ አንዳርጋቸው ሁሉ ተያዙ። ልጅ ምኒልክም ለቴዎድሮስ ገባ።

አጼ ምንሊክ በአፄ ተዎድሮስ ከተያዙ በኋላ ከአጼ ቴወድሮስ ልጆች ጋር እንደ ንጉስ ልጅ አደግዋል። ከአሰር አመት በሃላ ከ አጼ ቴውድሮስ የቁም እስር ካመለጡ በኋላ ወደ ሸዋ ተመልሰው በ 1865 የሸዋ ንጉስ ሆኑ ። በወቅቱ የኢትዮጲያ ንጉስ የነበሩት ንጉስ አጼ ዮሃንስ 4ተኛ መጋቢት 2 ቀን 1881 ዓ.ም በመተማ ጦርነት ሞቱ ።

ከዚህ በኋላ በ1881 ዓ.ም አጤ ዮሐንስ መተማ ላይ ከተሰው በኋላ የግዛቱ ሹማምንት ለምኒልክ ታማኝነታቸውን በማሳየታቸው ምኒልክ ንጉሰ ነገሥት ለመሆን ምንም የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ እርግጠኛ ሆኑ፡፡

በዚህም ምክያት ጥቅምት 25 ቀን 1882 ዓ.ም በዛሬው ቀን ከ 133 አመት በፊት በእንጦጦ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን በጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ ተቀብተው ‹‹ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው ነገሱ፡፡

ምንሊክ በንግስና ዘመናቸው የአድዋ ጦርነት ጣሊያን ድል ማደርጋቸው እና ለዘመናዊ ኢትዮጲያ መፈጠር ምክንያት ሆንዋል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-04