ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን የተመሰረተበት ዕለት

በአፍሪካ እግር ኳስ እንዲጎልበት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ መመስረት ሚናው ትልቅ ነው ።

በእግር ኳስ ኮንፊደሬሽኑ ምስረታ ደግሞ ኢትዮጲያዊው ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አስተዋጿቸው ታላቅ መሆኑ አይዘንጋም ።

ይህም የእግር ኳስ ኮንፊደሬሽን የተመሰረተው በዛሬው ቀን ከ66 አመት በፊት ነበር፡፡ የዕለቱን ከታሪክ ትኩረታችን ነው ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የተመሰረተው በዛሬው ቀን ከ66 አመት በፊት ነበር ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን ፣ ግብፅ እና ደበቡ አፍሪካ መስራች ሃገራት ነበሩ። ኢትዮጲያዊው ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ኮንፌደሬሽኑን ለ 14 አመት በፕሬዘድንተነት አገልግለዋል። በነጮች ጨለማው በተባለው አህጉር፣ ህዝቦቿ የባርነት ቀንበር በሚማምቅቁባት አፍሪካ አንድ የስፖርት ሻማ ብቅ አለ እሱም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ነበር ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በ1957 ካርቱም በዛሬው ቀን ምስረታውን አደረገ ።በምሰረታው ኢትዮጵያ ሱዳን፣ በግብፅ እና ደበቡ አፍሪካ ተሳታፊ ሃገራት ነበሩ ። ይህ ኮንፌዴሬሽን በአፍሪካ ምድር የተመሰረተ የመጀመሪያው አህጉራዊ ማህበር ነበር ። ኮንፊድሬሽኑ ከተመሰረት በኋላ ውድድሮችን ማዘጋጀት ጀመረ የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም በሱዳን ካርቱም ተካሂደ ። በወድድሩ ኢትዮጲያ ፣ሱዳን እና ግብጸ ተሳታፊ ሃገራት ነበሩ ። በዚህ ወድድር ደቡብ አፍሪካ ተስታፊ ለመሆን ብትቀርብም በአፓርታይድ ፖሊሲ ምክንያት ብሄራዊ ቡድኗ ነጭ ተጫዋቾችን ብቻ በመምረጧ ከወድድሩ እንደትወጣ ተደርጓል ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በዛሬው ቀን ለምሰረታ በቅቶ ዛሬ ላይ በአህጉሪቱ የሚገኙ ሁሉም ሃገራትን እንዲሳተፉ ማድረግ እንዲችል አንድ ታላቅ ኢትዮጲያዊ ሚናቸው ቀላል አልነበርም ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ። ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን CAF ምስረታ ላይ የአንበሳውን ድርሻ የተወጡ ታላቅ ሰው ናቸው ፡፡ ተቋሙንም ለ14 ዓመታት በፕሬዝደንት በብቃት መርተወታል ። ዛሬም ድረስ CAF የሚመራባቸው አብዛኞቹ ሕጎችም በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ክቡር አቶ ይድነቃቸው አፍሪካ በዓለም ዋንጫ የመካፈል መብት እንደታገኝ ከፊፋ ጋር ለብዙ ዓመታት ታግለዋል። የትንባሆና የአልኮል ማስታወቂያዎች በአፍሪካ ስታድየሞች እንዳይሰቀሉ ፣ እንደ ድርጅት አፓርታይድን በሰፋት ተቃውመዋል ፣ የአፍሪካ ዳኞች እና ኮሚሽነሮች የአለም አቀፍ ውድድሮች ልምድ እንዲቀስሙ አድረገዋል። ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለአፍሪካ እግር ኳስ ከሰሯቸው ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፊደሬሽን እና ለአፍሪካ እግር ኳስ ላበርከተቱ አስተዋጾ በሃገራቸው አንድ መታሰቢያ ባይቆምላቸውም በሞሮኮ ንጉሥ ሐሰን ዳግማዊ በተሰጠ መመርያ ግን በ1981 አም በካዛብላንካ የሚገኝ ስታዲየም በስማቸው እንዲሰየምላቸው ተደርጓል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2023-02-08