ሀገሬ ቲቪ

የሆሊውድ ንጉሱ ክላርክ ጋብል

ለዓለም የፊልም ኢንዱስትሪ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረከተ ነው። ዛሬ ላይ ከዓለማችን ቀዳሚ የፊልም መንደር የሆነው የአሜሪካው ሆሊውድ አሁን ላለበት ደረጃ ያበቃው እሱ ነው ይባላል።

ዘመን አፈራሽ ቴክኖሊጂዎችን ተጠቅሞ ከተለመዱት ወጣ ያሉ ፊልሞችን በዳይሬክቲንግና በትወናው ለዓለም አስተዋውቋል ። ይህም ተግባሩ አሁን ድረስ የሆሊውድ ንጉስ የሚል ስያሜ አሰጥቶታል ። ዊልያም ክላርክ ጋብል።

የዛሬዋ ቀን 1901 ይህ ሰው ወደዝች ምድር የመጣባት ቀን ናትና በዕለቱን ከታሪካችን ልንዳስሰው ወደድን ።

በሀገረ አሜሪካ ኦሀዮ ከተማ በእርሻ ስራ ከሚይተዳደሩ ቤተሰቦቹ የተወለደው ጋብል እናቱን በጨቅላ ዕድሜው በማጣቱ ከአባቱ ጋር ብዙ መከራዎችን ለመቀበል ተገዷል።

አባት የሚያገኘው ደሞዝ ብቸኛ ልጁን ለማሳደግ እየፈተነው ሲመጣም ጋብል የሁለትኛ ደረጃ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ስራ አለም ተቀላቀለ።

ከልጅነቱ ለትወና ባለው ፍቅር ከመምህራን ቅሬታ የሚቀርበበት ጋሊን አሁን ነጻነቱን አውጆ ከስራው ጎን ለጎን ጥበቡን የሚያወጣበትን መንገድ ይፈልግ ጀመር።

ከግዜያት በኋላም የአንጋፋዋ ተዋናይት ጆሴፊን ዲሎን የግል ጠባቂና ረዳት በመሆን ማገልገል የጀመረው ይህ ሰው በ1924ም ከተወዳጇ ተዋናይት ጋር በጋብቻ ተጣመረ ። በዚህ ግዜ ነበር የዛሬው የሆሊውድ ንጉስ ወደ ጥበብ አለሙ የመቀላቀል መንገዱ የተጀመረው።

ጋሊን በዝነኛው ተዋናይ የተፈጠረለትን ዕድል ተጠቅሙ የተለያዩ ፊልሞች ላይ ትንንሽ ገጸባህሪያቶችን በመተወን ታላላቅ የፊልም ባለሞያዎች አይን ውስጥ በመግባት ታላቁን የአሜሪካ የፊልም ኢንዱስትሪ ሆሊውድን ተቀላቀለ።

የእርስበርስ ጦርነት መዘዞችን ፤ የሀገራት ታሪክ እንዲሁም በበርካታ የፍቅር ፊልሞች ላይ በመሳተፍ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሆሊውድ አለኝ ከሚለው የፊልም ባለሞያዎች አንዱ ሆነ።

ለሚወደው ጥበብ ራሱን አሳልፎ የሰጠው የሆሊውድ ንጉሱ በሰወች ልብ ውስጥ እንደተወደደ በተወለደ በ 59 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በዮሴፍ ከበደ
2023-02-01