ሀገሬ ቲቪ

የአውዳሚው ሃይድሮጅን ቦንብ ግልጽ የኾነበት

ሀይድሮጅን ቦምብ አውዳሚነቱ በትልቁ የሚወራለት የጦር መሳሪያ ነው። በጃፓን ላይ በመጣሉ ትልቅ ሰቆቃን ካደረሰው የአቶሚክ ቦምብ በመቶ እጥፍ የሚልቅ ጉዳት ያደርሳል ይባልለታል።

በጊዜው ደግሞ አሜሪካ እና ሶቭየት ህብረት የጦር መሳሪያ የበላይነት ፉክክር ውስጥ ነበሩ። ዩናይትድ ስቴትስ ሶቭየት ህብረት በካዛክስታን የሙከራ ስፍራዋ የአቶሚክ ቦምብን በተሳካ ሁኔታ ስታፈነዳ አሜሪካ የኒውክሌር የበላይነቷን ማጣት ተሰምቷታል።

በአሜሪካ የኒውክሌር ፕሮግራም የሚሳተፍ ከፍተኛ የጀርመን ውልደት ያለው ተመራማሪው ክላውስ ፉች የሶቭየት ህብረት ሰላይ ነው የሚል ጥርጣሬን በአሜሪካ እና እንግሊዝ ላይ አሳድሯል።

በዚህ ስጋትም የአሜሪካ የትኛውም የጦር መሳሪያ ማበልጸግ ዕቅድ ሶቭየት መረጃው አላት በሚል ስጋት አሜሪካ የጀመረችውን በድብቅ ሃይድሮጅን ቦምብ ማበልጸግን በይፋ እንደምትደግፍ ግልጽ አደረገች።

ይህ የሆነው ሶቭየት በተሳካ ሁኔታ የአቶሚክ ቦምብ ሙከራን ካደረገች ከአምስት ወራት በኋላ በ1942 ዓ.ም. በዛሬዋ ነበር።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ሃሪ ቱርማን የዓለማችን አውዳሚውን ቦምብ ማበልጸግን በጦር መሳሪያ የበላይነት ፉክክሩ ቀዳሚ ለመሆን በከፍተኛ ሁኔታ እንድሚደግፉ አስታወቁ።

ኋላም በ1953 ዓ.ም. በፓሲፊክ የማርሻል ደሴቶች ላይ አሜሪካ የመጀመሪያውን እና ቀዳሚውን ማይክ የተሰኘውን አውዳሚውን የሀይድሮጅን ቦምብን ሞከረች። ይሄው ሙከራ ደሴቷን ያወደማት ሲሆን ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥንም አስከትሏል።

ደሴቷ እንድትተን ያደረገ ሲሆን በደመናነት የደሴቷ አካላት ወደ ከባቢ አየር እንዲቀላቀሉ አስገድዷል። ይሄው አስፈሪ ቦምብ እውነትን አስፈሪ ነው እንዲባልለትም አድርጓል።

ሶቭየት ህብረትም ይሄንንው አደገኛ ሀይድሮጅን ቦምብ ከሶስት ዓመታት በኋላ ታጥቀዋለች። ዓለም የምትጨነቅበትን ይሄን ቦምብ በሁለቱ ኃያላን እጅ አለ።

በአብርሃም በለጠ
2023-01-31