ሀገሬ ቲቪ

በዚህ ዓመት በአማራ እና አፋር 200 ት/ቤቶች እንደሚገነቡ ተገለጸ

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት 200 ት/ቤቶች በአማራ እና አፋር ክልሎች እንደሚገነቡ አስታወቀ።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አመለ ወርቅ ህዝቅኤል በት/ቤት ግንባታዎቹ መንግስታዊ ያልሆኑ የረድኤት ተቋማት እያገዙ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሊገነቡ ከታቀዱት ት/ቤቶች የአምስቱ ግንባታ ተጀመሯልም ተብሏል።

ህብረተሰቡ በ9222 ለትምህርት ተቋማቱ ግንባታ ተስትፎ እንዲያደርግም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ አርኪቴክቶች ማህበርም ሊገነቡ የታሰቡትን ት/ቤቶች ዲዛይን አጠናቆ ማስረከቡ ተገልጿል።

በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል በሺዎች የሚቆጠሩ ት/ቤቶች በጦርነት መውደማቸው ይታወሳል።

በብሩክ ያሬድ
2022-11-04