የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በአራት ቀናት ውስጥ 30 ሺ ለሚኾኑ ዜጎች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
ድጋፉ በሰቆጣ ለሚገኙ እና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ነው ተብሏል።
ድጋፉ የምግብ ውጤቶች ሲኾን 18 ሺህ ለሚኾኑት ደግሞ ጠቃሚ የቤት ዕቃዎችን ለግሻለሁ ማለቱን ከማኀበራዊ ትስስር ገጹ ተመልክተናል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-04
