ሀገሬ ቲቪ

በእስራኤል ምርጫ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ፓርቲ አሸነፈ

በእስራኤል በተካሄደ ምርጫ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያን ኔታንያሁ የሚመራው ጥምር ፓርቲ ማሸነፉ ተገለጸ።

ይፋ በተደረገው የእስራዔል ምርጫ ውጤት በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ የሚመራው ጥምር ፓርቲ ከ120 የእስራዔል ፓርላማ መቀመጫ 64 መቀመጫዎችን ማሸነፉ ተገልጿል።

ከ64ቱ መቀመጫዎች ውስጥ የኔታንያሁ ፓርቲ የሆነው ሊኩድ 32 መቀመጫዎችን አጊንቷል ተብሏል ።

የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ዳግም ወደ ስልጣን ከተመለሱ በሀገሪቱ አቃቤ ህግ ለተመሰረተባቸው የሙስና ክስ እልባት ሊሰጥበት እንደሚችልም ተገልጿል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-11-04