ሀገሬ ቲቪ

የዓለም ሙቀት መጨመር ዓለማችንን ለከፍተኛ ስጋት ዳርጓታል ተባለ

27ኛው የአየር ንብረት ለውጥ አለምአቀፍ ጉባኤ በግብጽ ተጀምሯል። የግብጿ ሻርም-አል ሼክ ደግሞ ለጉባኤው የተመረጠች ቦታናት።

የአየር ንብረት ለውጥ በአለማችን ከፍተኛ ስጋትነቱ በየግዜው እየጨመረ ነው ።የለፉት ስምንት አመታትን መሰረት አድርጎ የተካሄደው ጥናት አንደሚያሳየው ድርቅ የሙቀት መጨመር ከመጠን ያለፈ ዝናብ የሚያስከትለው ጎርፍ ዓለማችንን በአየር ንብረት ለውጥ እንድትናጥ አድርጓታል።

የተባብሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ኤጅንሲ ባሳልፍነው እሁድ ባወጣው ሪፖርት መሰረት የዓለማችን ሙቅት ከትክክልኛው የሙቅት መጠን 1.5C (2.7F) በአማካኝ መጨመሩን ገልጿል።

ይህም በአውሮፓ ሳይቀር በታሪኩ ያልታየ ከፍተኛ የውሃ እጥረትና ድርቅ አጋጥሞታል።አፍሪካም የዚህ በትር ዋነኛ ቀማሽ ነች።

የግብፁ ጉባኤ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በከፍተኛ ሁኔታ ለችግር ተጋላጭ ከሆኑ አሁጉራት ቀዳሚ የሆነችው አፍሪካ ይህን እንድትቋቋም ቃል የተገባላትን ድጎማ እንዲተገበር የሚያስችል ውሳኔ ማስወሰን ዋነኛ አጀንዳ ነው።

በተባበሩተ መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለወጥ ኃላፊ የሆኑት ሲሞን ስቲል ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት ይደረጋል የተባለውን ድጎማ ለዓመታት ሲቃዎሙ የነበሩ አሜሪካ እና ሌሎች ባለፀጋ ሀገራት አሁን አሁን ላይ ሀሳባቸውን መለወጣቸው እና የበሰል እና ጠንካራ ሀሳብ ይዘው መገኘታችው የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በዚህ ጉባኤ ላይ የአፍርሪካ ሀገራት እየተስተዋለ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ለዜጎቻቸው ከወዲሁ ለመላመድ እና የታዳሽ የኃይል ምንጮቸን በሚጠቀሙባቸው መንገዶች ላይ ይመከርበታልም ተብሎ ይጠበቃል።

የተባብሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ኤጅንሲ ባወጣው ሪፖርት፤ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ባልዋለችበት የምትቀጣው አፍሪካ የሚገኙ በባህር ዳርቻዎች እና ደሴቶች ላይ የሚኖሩ 116 ሚሊየን የሚልቁ ሰዎች የባህር ከፍታ መጨመር ስጋት ከፊታቸው ተደቅኗል።

ይህቺው ፈተናዋ የበዛ አህጉር አስከ ፈረንጆቹ 2050 ከአየር ንብረት ጋር የተገናኙ ጉዳቶችን ለመቀነስ እንድትችል በየዓመቱ ከ 50 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልጋት የድርጅቱ ሪፖርት ይጠቁማል።

እናም የሻርም አልሼክ ጉባኤ ይህ ፈንድ ከቃል በላይሆኖ ተግባር ላይ እንዲውል ሀብታም ሀገራት ተጨባጭ የለውጥ ውሳኔ እንዲወስኑ ያደርጋልም ተብሎ ይጠበቃል ።

ከ40,000 ሰዎች በላይ እየተሳተፉበት የሚገኘው በአፍሪካዊቷ ሀገር ግብፅ እየተካሄደ የሚገኝው የአየር ንብርት ለውጥ ጉባኤ ከአየር ንብረት ለውጥ በተጨማሪ፤ በአለም ላይ እየተስተዋል ስላለው የዋጋ ንረት፣ የምግብ እጥረት፣ በአለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ስለሆነው የዪኩሬን እና የሩሲያ ጦርነት፣ የሃይል አቅርቦት እጥረት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይመከርበታል ተብሏል ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

በማህሌት አማረ
2022-11-07