በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ካልፉ ዘመን አይሽሬ ከያኒያን መካከል እርሱ ቀዳሚው ነው። አድናቂዮቹም ይሉታል “የምስራቁ ዋርካ” የተወለደበትን ምስራቅ ኢትዮጲያን በማስታወስ ።
ድምፃዊው ምንም እንኳን በርካታ የሙዚቃ ስራዎቹን በኦሮምኛ ቢጫወትም እርሱ ግን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጭምር በተጫወታቸው ሙዚቃዎቹ የሚታወስ ከያኒ ነው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ።
በወረሃ ግንቦት 1940 ዓ.ም. በድሬ ዳዋ የተወለደውን ሙዚቀኛው ብዙዎች አሊ ቢራ በሚለው ስም ይወቁት እንጂ ወላጆቹ ያወጡለት አሊ መሐመድ ሙሳ ነበር።
አሊ ቢራ ለአባቱ አንድ ልጅ ቢሆንም ከእናቱ ወገን የሚወለዱ በርካታ እህትና ወንድሞች ነበሩት ።የአሊ አባት ልጃቸው የእንጨት ባለሙያ እንዲሆን ቢፈልጉም እርሱ ግን ለሙዚቃ የሸፈተ ነበር ።
አርቲስት አሊ ቢራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በድሬዳዋ ከተማ ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በአዲስ አበባ ካቴድራል ትምህርት ቤት ተከታትሏል። አሜሪካ ሀገር በሚገኘው የሳንታ ሞኒካ ኮሌጅም የሙዚቃ ትምህርቱን እንደ ተማረ ይነገራል።
በትምህርት ቤት፣ መምህር በሌለበት ጊዜ አልያም በእረፍት ሰዓት በማንጎራጎር እና በመደነስ ሌሎችን ማዝናናት ያስደስተው ነበር።
አርቲስት አሊ ቢራ የኦሮሞን ሙዚቃ ለማስተዋወቅ ዓላማ ያደረገ የባህላዊ ሙዚቃ ቡድን “አፍረን ቀሎ”ን በ1954 ዓ.ም በመቀላቀል ነበር የሙዚቃ ስራውን አሃዱ ያለው ።
ቤተሰቡ ያወጡለት አሊ ሙሃመድ ሙሳ የሚለው ሰሙም ወደ አሊ ቢራ የትቀየርበትም አጋጣሚ እዚ ላይ ነበር ተፈጠረው ።
በቡድኑ ውስጥ ሌላ ዓሊ የተባለ ልጅ በመኖሩ ሁለቱን ለመለየት መጀመሪያ ከሚያዜመው "ቢራ ዳ ባሬ" ዘፈን ተወስዶ "ዓሊ ቢራ" የሚለው ሰም እንደተሰጠው ይነገራል።
አርቲስ አሊቢራ የሙዚቃ ሰራውን እና ፍቅሩን በደንብ ለመወጣት ሲል በ 1957 አዲስ አበባ በመምጣት የክቡር ዘበኛ ባንድን ተቀላቀለ።
አርቲስ አሊ ቢራ የሙዚቃ ሰራን ለሶስት አመታት በክቡር ዘበኛ ከሰራ በኋላ ከሙዚቃው በውጣት ምድር ባቡር በመቀጠር፣ አዋሽ ተመድቦ መስራት ጀመረ። ሙዚቃ የነብሰ ጥሪ የሆነው አርቲስት አሊ ዳግም ከ 3 አመት በኋላ ወደ ሙዚቃው ተመለሰ ።
ከ አዋሽ የተመለሰው አርቲስት አሊ በአዲስ አበባ የምሽት ክበብቦች እና መድርኮች ላይ ሰራወን ያቀርብ ጀመር። ከዚህ በኋላም በ1967 ዓ.ም ከአዱ ቢራ ባንድ የመጀመርያውን አልበም አሳተመ።
በ1970ዎቹ የአርቲስት አሊ ቢራ ዝና ጣርያ የደረሰበት ነበር።በዚያን ጊዜም በተደጋጋሚም የሙዚቃ አልበሞቹን አሳትሟል። በኦሮምኛ፣ በሶማልኛ፣ በአማርኛ እና አረብኛ የሚዘፍነው አርቲስት አሊ ሁሉንም ቋንቋዎች ሲጫወት የአድናቂቆቹን ልብ ይገዛ ነበር ።
አርቲስት አሊ ቢራ ሙዚቃን ማቀንቀን ከጀመረበት እንከኖረበት ድረስ ከ 267 በላይ ሙዚቅዎችን ተጫውቷል ።ከሙዚቃ መጫወት በተጨማሪ ሙዚቃዎቹን ራሱ ያቀናብራል። ጊታር፣ ኪቦርድ፣ ፒያኖ፣ አኮርዲዮን እና ሐርሞኒካ አሳምሮ ይጫወታል።
ለሌሎች ሙዚቀኞችም ቢሆን የግጥም እና የዜማ ሰርዎችን ሰጥቷል ። አርቲስት አሊ ቢራ በሕይወት ዘመኑ ከ50 በላይ ሽልማቶቹን ተቀበሏል። ከዚህም በተጨማሪ ፣ ከጅማ ዩኒቨርስቲ እና ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲም የክብር ዶክተሬቶችን ተቀብሏል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-07
