የፌደራል መንግስት እና የሕወኃት ወታደራዊ አዛዦች በኬንያ ሕወኃት ትጥቅ በሚፈታበት ሂደት ላይ እየመከሩ መሆኑ ተገለጸ።
ይህንን የገለጹት በድርድሩ አደራዳሪ የነበሩት ኡሁሩ ኬንያታ ናቸው። ኬንያታ በቀጣይ በመቀሌ እንደምንገናኝ ብሎም በአዲስ አበባ በጋራ ስምምነቱን እንደምናከብረው ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
የደቡብ አፍሪካውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ ላይ ለመመካከር ስምምነት አድርገው እንደነበር ይታወሳል።
የአፍሪካ ሕብረት ተወካይ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የፌደራል መንግስት እና ሕወኃት በጉዳዩ ላይ የስልክ ንግግር ማድረግ መጀመራቸውን ቀደም ብለው አስታውቀዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-11-07
