ሀገሬ ቲቪ

ኢሰመኮ ያላግባብ ታስረዋል ያላቸው የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ዳኞች ተለቀቁ

ኢሰመኮ ያላግባብ ታስረዋል ያላቸው 3 የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች መለቀቃቸውን አስታወቀ።

ዳኛ ደሳለኝ ለሚ ፣ ሙሀመድ ጅማ እና አብዲሳ ዋቅጅራ በሕግ የተሰጣቸው ልዩ ጥበቃ መብት ሳይነሳ ከወረዳ ፍርድ ቤት ተሰጥቷል በተባለ የእስር ትእዛዝ ከሥራ ገበታቸው ላይ ተነስተው መታሰራቸውን ኢሰመኮ ገልጾ ነበር ።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕ/ት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊም ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ያለመከሰስ መብታቸው " ከተነሳ በኃላ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበው ነበር።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ዳኞቹ ከተፈፀመባቸው የዘፈቀደ እስር ቢለቀቁም ባለስልጣናት ግን ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አለባቸው ብለዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-11-07