ሀገሬ ቲቪ

ቪክቶሪያ ሐይቅ ውስጥ በተከሰከሰው አውሮፕላን የሟቾች ቁጥር 19 ደረሰ

ቪክቶሪያ ሐይቅ ውስጥ በተከሰከሰው የታንዛኒያ ንብረት በሆነው የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 19 መድረሱን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር አስታወቁ ።

መነሻዋን ከዳሬ ሠላም ያረገችው አውሮፕላን ወደ ማረፊያዋ ቡኮባ በተቃረበችበት ሰዐት በተፈጠረ ከባድ የአየር ጠባይ መከስከሷ ተገልጿል ።

አውሮፕላኗ 39 ተሳፋሪዎች ሁለት አብራሪ እንዲሁም 2 የበረራ ሰራተኞችን ጭና ነበር። በአደጋው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዐት ድረስ 19 ሰዎች ሲሞቱ 24ቱ የህክምና ክትትል ላይ መሆናቸውን አልጄዜራ ዘግቧል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-11-07