ሀገሬ ቲቪ

የእስረኞችን ክስ ማቋረጥ አንድምታው

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል ከቀናት በፊት የተፈቱት የፖለቲከኛ እስረኞች ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረገውሁለት መሰረታዊ ዓላማዎችን ለማሳካት ነው እንደሆነ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋሉ ማህበረ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ከእልህና ከመጠፋፋት ፖለቲካ በራቀ፣ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ሊያረጋግጥ በሚችለው በሀገራዊ አካታች ዲሞክራሲዊ ስርዓት ለመፍታት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታን ለመፍጠር አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪ ዋስትና ያለዉ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና፣ ጠንካራ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለመገንባት እና ሉዐላዊ አንድነትን ከአደጋ ለመታደግ ተብሎ የተወሰደ ፖለቲካዊ እርምጃ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ ካለፉት ቁርሾዎቻችንና ካሳለፍናቸው መከራዎች አኳያ በመንግስት ሰሞነኛ ዉሳኔ ላይ ጥርጣሬዎች መነሳታቸው ተገቢ አይደለም ባይባልም ከራሱ ከመንግስት ባህሪ ህዝባችን እምነቱን ማሳደር እንዳለበት ጠቁመዋል መንግስት ክስ አቋረጠ እንጂ ግለሰቦቹ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ነፃ ናቸው አለመባሉን አንስተዋል፡፡ ክሳቸው የተቋረጠላቸው ወገኖችም ካለፈው የጥፋት መንገድ ተምረው የተሻለ ፖለቲካዊና ማህበራዊ አስተዋፅኦ ለማበርከት እንዲችሉ ዕድል የተሰጣቸው ስለሆነ ህዝባቸውንና ሀገራቸውን ይክሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-12