ሀገሬ ቲቪ

የእስራኤል ነዋሪዎች በኔታኒያሁ መመረጥ ከፍተኛ ተስፋ እንዳላቸው ተጠቆመ

በእስራኤል ምርጫ በቤንያሚን ኔታንያሁ መመረጥ የእስራኤል ነዋሪዎች ከፍ ያለ ተስፋን ይዘዋል ተባለ።

በዌስት ባንክ ከፍተኛ ቦታዎች የሚኖሩ የሀገሪቱ ዜጎች ናቸው በኔታንያሁ መመረጥ ደስተኛ መሆናቸው የተገለጸው። ነዋሪዎቹ የእስራኤል መንግስት በዌስት ባንክ ዜጎቹን የማስፈር ዕቅድን እንዲገፋ ፍላጎት አላቸው።

ለዚህም ኔታንያሁ ይሰራሉ ብለው ተስፋቸውን ጥለዋል። በዌስት ባንክ 450 ሺህ ያክል እስራኤላውያን ሲኖሩ 3 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድራሉ።

በአብርሃም በለጠ
2022-11-07