መተጋገዝ፤ በምድር የመኖራችን ዋነኛ ምክንያት ነው። በዚህ አድካሚዓለም ውስጥ ስንኖር በግላችን ጥረት ብቻ የምንሻገራቸው ፈተናዎች የሉንም።
አወቅነውም አላወቅነውም፤ ትላንት ባልናቸው የፈተና ግዜዎቻችን ውስጥ የሆነ ያገዘን አካል አለ።
ዛሬ ድር ቢያብርት አንበሳ ያስር የሚለውን የወንዚአችንን አባባል ሀቅ ነው የሚያኝ ታሪክ አገኘን እና ልናጋራችሁ ወደድን።
ከሰሞኑ ፊሊፒንን ከባድ አውሎነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ቅጽበታዊ ጎርፍ አስከትሎ ከ100 ያለነሱ ዜጎቿን ስልለመቅጠፉ በመገናኛ ብዙኃን ተሰምቷል።
በዚሁ ጎርፍ ሳቢያም በርካታ ቤቶች አሉ ከመባል ወደ ነበርነት ተለውጠዋል። ንብረት ወድሟል በርካቶች ካለመጠለያ ቀርተዋል።
በዚህ ሁሉ መሃል በርከት ያሉ ወጣቶች አንድ አነስ ያለች ቤትን ከስር መሰረቷ ተሸክመው በጎርፍ የተሞላ ወንዝን ሲያቋርጡ ታዩ።
ከ40 የሚልቁት እነዚሁ ወጣቶች የጎረቤታቸውን ቤት በትከሻቸው ተሸክመው ከወንዙ ማዶ ማሻገራቸው በርካቶችን አጀብ አሰኝቷል።
ለህይወታቸው ያልሳሱት ወጣቶቹ ለጎርፍ ተጋላጭ ቦታላይ የነበረውን ቤት፤ የሚወርደው ዶፍ ዝናብ፤ የሞላው ወንዝ ሳይበግራቸው ከፍ ወዳለው ቦታ አሻግረውታል።
ታዲያ በዚህ ውስጥ ለአመል ያህል እንኳን የተጫረ ሳይኖር በሰላም ቤቱን አሻግረውታል።
ታዲያ አንድ የመንደሩ ሰው እንዳለው ከሆነ ፤ ድርጊቱ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ያውቃሉ፤ በዚህ ያለነው ሰዎች እርስ በእርስ እንደጋገፋለን። ትንሽዬ መንደር ናት ያለችን፤ በዚህ ያለ ሰው እንደ ቤተሰብ ነው የሚታየው።
የቤቱ ባለቤቶች ዝናቡ ሲጀምር እና ደራሹ ጎርፍ ሲመጣ እራሳቸውን አድነዋል። ታዲያ ቤታችንስ ያሉት እነዚሁ ቤተሰቦች ቤታችንን ከጎርፍ አስጥሉልን ሲሉ የተማጽኖ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ፍሊፒንስ ደጋግሞ ለሚከሰት ሞቃታማ አውሎ ንፋስ የተጋለጠች ሀገር ነች፤ ይህም ሀገሪቱን ደጋግማ ለከባድ ዝናብ እና እና ድንገተኛ ጎርፍ እያጋለጣት ዘመናትን ተሻግሯል።
ከ10 ቀናት በፊት በተከሰተው በዚሁ ከባድ ዝናብ እና ጎርፍ ከ100 ያላነሱ ሰዎቿንም አጥታለች። ፍሊፒንስ ዛሬን እንዲህ ባለ ቀና ልብ ባላቸው ዜጎቿ ታግዛ አለች።
በሳምሶን ገድሉ
2022-11-07
