ሀገሬ ቲቪ

በአየር ንብረት ለውጥ የሚደርሰው ጉዳት ለመቀነስ 2 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋል

አለም ዛሬም ድረስ በአየር ንብረት ለወጥ ሳቢያ ዋጋን ትከፈላለች ። የሙቀት መጨመር እና የጎርፍ አደጋ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈም ይገኛል ።

የዚሁ ሁሉ ገፈት ቀማሽ ደግሞ በማደግ ላይ የሚገኙ ሃገራት ሃገራት ናቸው። የአየር ንብረት ለወጥን አስመልክቶ የሚካሄድው ጉባኤ ዛሬም ቀጥሏል።

በ2030 ታዳጊ ሀገራት የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እና የአየር ንብረት ለወጥ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቋቋም እንዲረዳ 2 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ አዲስ መረጃ ይፋ ተደርጓል ።

ድሀ ሀገራት ከቅሪተ አካል የሚያገኙትን የሃይል ፍላጎት እንዲያቆሙ ፣ በታዳሽ ሃይል እና በሌሎች ዝቅተኛ ካርቦን ቴክኖሎጂዎች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እና የአየር ጸባይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቋቋም ገንዘቡ እንደሚያስፈልግ የእንግሊዝ እና የግብፅ መንግስታት በጋራ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

በጉባኤው እንዲ ይባል እንጂ በተለያዩ የአየር ንብረት ለወጥ ጉባኤዎች ለታዳጊ ሃገራት እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ እስክ 2020 ቢያንስ 100 ቢሊየን ዶላር በአመት እንደሚያገኙ ቃል ቢገባላቸውም እስከ አሁን ሳይሳካ ቀረቷል ።

ኒኮላስ ሳተርን የተባለ አየር ንብረት ለውጥ ኢኮኖሚስት የ2006ቱን የአየር ንበረት ለወጥ ጉባኤ አስታውሶ ባወጣው ጸሁፍ ።

የበለፀጉ አገሮች ከፍተኛ መጠን ያለው የቴክኖሎጂ ወጤቶችን መጠቀም በታዳጊ ሃገራት ሊያከትል የሚችለውን ከፍተኛ ተጽዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለግል ጥቅማቸው ከመሰራት ይልቅ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሊሰሩ ይገባል ያላል ።

ሳተርን ሲቀጥል በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ሊከሰት የሚችለው የሃይል ፈላጎት እና ፍጆታ አብዛኛው የሚሆነው በታዳጊ እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ነው።

ስለዚህ ከበካይ ጋዝ እና ለአየር ንበረት ለውጥ ዋና ምክንያት በሆኑ የሃይል ምንጮች ላይ ጥገኛ በመሆን የአየር ንብረት ለውጥን ማስወገድ አይቻልም ይላል ሰላዚህ አለም በአንከሮ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ካልሰራ በሀብታም ሆነ በድሃ አገሮች በቢሊዮን የሚቆጠሩ ህይወቶችን እና ሃብቶችን እየጎዳ እና እያወደመ ነው ሚቀጥለው ።

በግብጽ እየተካሄድ ባለው የኮፕ 27 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ንግግር ያደርጉት የግብጹ ፕሪዘዳንት ለአየር ንበረት ለውጥ አሁን የተግባር ግዜ ነው ብሏል።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ፤ ዓለማችን በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከነበረችበት የሙቀት መጠን አሁን በ1 ነጥብ 2 ዲግሪ ሴልሺዬስ ገዳማ ጨምራለች። ወደ አየር ንብረት የሚለቀቀው የካርበን ዳይኦክሳይድ መጠንም በ50 በመቶ ጨምሯል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-08