የአርቲስት አሊ ቢራ ሥርዓተ ቀብር በትውልድ አካባቢው ድሬዳዋ ተፈጽሟል።
አስክሬኑ ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ዛሬ ማለዳ ወደ ወዳጅነት አደባባይ የተሸኘ ሲሆን በስፍራውም የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሥልጣናት በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል።
በስተመጨረሻም አስክሬኑ ወደ ትውልድ ከተማው ድሬ ዳዋ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተሸኝቷል፤ ስርዓተ ቀብሩም በድሬዋዳዋ ከተማ ተፈጽሟል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-08
