በምዕራብ ኦሮሚያ ነቀምት ከተማ ገብተው የነበሩ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን ከነዋሪዎች ሰምቻለሁ ሲል ዶይቼ ቬሌ ዘግቧል።
እሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በአሸባሪነት የተፈረጀው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩት።
ታጣቂዎቹ በከተማዋ ሶስት አቅጣጫ ዘልቀው በመግባት ከማለዳ አንስቶ የጀመሩት የተኩስ ልውውጥ እስከ እኩለ ቀን ቀጥሎ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ከዚያ በኋላ የቡድኑ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው እንደወጡ ተሰምቷል። በተኩስ ልውውጡ ሰለባ የሆኑት በርካታ ንጹሃን ሊኖሩ እንደሚችሉም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በተኩስ ልውውጡ ከዞን ማረሚያ ውጪ ያሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ እስረኞች መለቀቃቸውንም ዘገባው ገልጿል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-08
