ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የብረት ብየዳ ስልጠና ማዕከል በመሆን ሰርተፍኬት ተቀበለች።
በቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት፣ የብረት ብየዳ ስልጠና ማዕከል፤ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የብረት ብየዳ ኢንስቲትዩት፤ ብቁ የብረት ብየዳ ስልጠና ማዕከልነት የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት ተበርክቶላታል።
ዕውቅናው በብረት ብየዳ ሙያ ለሰለጠኑ ዜጎች የስራ እድልን የሚያሰፋና በዓለም ገበያ ተፈላጊ እንዲሆኑ የሚያደርግ መሆኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በማህበራዊ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-11-08
