
ዩጋንዳ የመጀመሪያውን ሳተላይት ወደ ጠፈር በተሳካ ሁኔታ ማምጠቋን አስታወቀች። በሶስት ዩጋንዳዊያን እና ጃፓናዊያን ኢንጅነሮች የተሰራችው መንኩራኩር ፒርል አፍሪካ ዋን የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቷታል።
ኢራን በሚገኝ የሳተላይት ማስወንጨፊያ ወደ ጠፈር መላኳን ኢስታፍሪካን ኒውስ ዘግቧል። ሳተላይቷ ከጠፈር በቀጥታ በአየር ሁኔታ ትንበያ፣ በመሬት፣ በውሃ አካላት፣ ማዕድን እና ግብርና ክትትል ላይ መፍትሄ የሚሰጡ የምርምር እና የምልከታ መረጃዎችን እንደምታቀርብ የዩጋንዳ ሳየንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተናግሯል።
ይህም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ከህዋ የሚላኩ መረጃዎች ሀገሪቱን በበርካታ ዘርፎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላታል ተብሏል።
በማህሌት አማረ
2022-11-08