ሀገሬ ቲቪ

በሙቀት መጠን መጨመር እስካሁን 15 ሺሕ ሰዎች ሞተዋል

እየተገባደደ ባለው የፈርንጆቹ 2022 በሙቀት መጠን መጨመር ምክንያት 15 ሺሕ ዜጎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጀት አስታወቀ።

እንደ አብነትም በስፔን 4 ሺህ ዜጎች ከፍተኛ በሆነ የሙቀት መጠን ሞተዋል። ጀርመን 4,500 ዜጎቿን አጥታለች።

በፖርቹጋል ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች እንዲሁም በእንግሊዝ ከ 3ሺህ በላይ ዜጎች ከፍተኛውን የሙቀት መጠን መቋቋም ባለመቻላቸው ሕይወታቸው አልፏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-08