ሀገሬ ቲቪ

አልበርት አንስታይን የኖቤል ሽልማት ያገኘበት ቀን

የዛሬዋ ቀን በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተጽዕኖ ፈጣሪው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን ባዳበረው የፎቶ ኤሌክትሪክ ውጤት የኖቤል ሽልማትን ያገኘባት ቀን ናት።

በዛሬዋ ዕለት 1914 ዓ.ም ። ውልደቱ በ1879 በጀርመን ሲሆን የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በዛው አጠናቋል ። በአንድ ወቅት አባቱ በሙኒክ ከተማ የከፈተው ንግድ ለኪሳራ በመዳረና ወደ ጣሊያን ሀገር በመሰደዱ የተነሳ ጀርመን ሀገር ብቻውን የቀረው አይንስታይን እንደ ቀድሞው ለትምህርቱ ትኩረት መስጠት አልሆነለትም።

ለሂሳብ እና ፊዚክስ ልዩ ፍቅር ያለው ይህ ሰው ሁለትኛ ደረጃ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ መረጃዎቹን ይዞ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ድግሪ ለመውሰድ በስዊዝ ዙሪክ ከተማ የምዝገባ ማመልከቻውን አስገባ ።

ታዲያ ምንም እንኳን ትምህርቱን ያላጠናቀቀ ቢሆንም ዙሪክ ከተማ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ የሚፈትኑትን የመግቢያ ፈተና ካለፈ ሊማር እንደሚችል ይነግሩታል። አንስታይንም ሁለትኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በከፍተኛ ነጥብ ካጠናቀቁ ታላላቆቹ ጋር ፈተናውን ለመውሰድ ገባ ።

ፈረንሳይኛ ፣ ሒሳብ ፣ ፊዚክስ ፣ ታሪክ፣ ጆግራፊ እና ሙዚቃን ያካተተው ፈተናው ለ አንስታይን ከባድ ነበር ። ጊዜው ደረሰና የፈተና ውጤቱ ወጣ ይህ ታዲ ልጅ በወቅቱ በ ሂሳብና ፊዚክስ አንቱታን ያተረፉ ታላላቆቹን በመብለጥ ከ ክፍሉ ስሙ ከላይ ተጻፈ ።

ነገር ግን ሌሎቹ የትምህርት አይነቶች ለ አንስታይን እንግዳ ነበሩን አልታሳካለትም ። ወደ ኮሌጅ ለመግባት ያደረገው ጥረት በታሪክና በጂዮግራፊ ትምህርቶች መበላሸት ሳይሳካ ቀረ።

ይህን ፈተና በመውደቁ የተበሳጨው አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ድጋሜ ገብቶ በማጠናቀቅ ያኔ ፈልጎት ያልተሳካለትን ፈተና በድጋሜ ወሰደ ።

"ከትላንት እንማራለን፣ ዛሬን እንኖራለን፣ ስለነገም ተስፋ እናደርጋለን" የሚለው አንስታይን በመጨረሻ ህልሙን እውን አድርጎ በኮሌጁ ለመታቀፍ በቃ። የኮሌጅ ቆይታውም አስገራሚ የነበረ ሲሆን 10 በመቶ ጊዜውን ለጥናት 90 በመቶውን ደግሞ ለተግባራዊ ምርምር በቤተ ሙከራ ውስጥ ማሳለፍ ጀመረ ።

በትምህርት ቤት ውስጥ የሳይንስ ምርምሮችን በማድረግም በተለያዩ ጊዜያት ተሸላሚ ነበር። በመጨረሻም በ19,00 የኮሌጁ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን የኤልክትሪክ ምህንድስና ድግሪውን ጫነ።

አንስታይን እዝች አለም በኖረባት ዕድሜ በርካታ ፈጠራዎችን ብሎም ቀመሮችን ለአለም አበርክቷል ። ብዙዎች አሁን ላይ ሆነው የ አንስታይንን ፈጠራዎች ሲገመግሙ ይህ ሰው አራት የፊዚክስ የኖቤል ሽልማቶችን ማግኘት ይችል ነበር ይላሉ።

እውነታው ግን አንዱንም ያገኘው ለስምንት ጊዜ ያህል በዕጩነት ከቀረበ በኋላ ነው ። ምክንያቱ ደግሞ የኖቤል ሽልማትን የሚሸልመው ኮሚቴ አባላት ለ250 ዓመታት ተንሰራፍቶ የነበረውን የፊዚክስ ዕሳቤ የለወጠውን የአንስታይን ንድፈ‐ሀሳብ ሊረዱት ባለመቻላቸው ነበር ፡፡

በወቅቱ የሱን ቀመሮች ይረዱ የነበሩ ሰወች ይህ ሰው ከመሞቱ በፊት የሚገባውን ክብር ስጡት እያሉ መወትወት ጀመሩ ።

የአይንስታይንን ስራ በተለይ የአንጻራዊነት ንድፈ‐ሀሳብን እንዲገመግሙ የተመደቡት የፊዚክስ ሊቃውንት ምንም አይነት መደምደሚያ ላይ ባልደረሱበት ሁኔታ የፊዚክስ ዘርፍ ሸላሚው ኮሚቴ ከአይንስታይን ሌሎች ስራዎች መሃል አንዱ የሆነውን የ Photoelectric Effect ስራውን ተገንዝቦ ሌላውንም አክሎበት በስተመጨረሻ በ 1914 ዓ.ም በዛሬዋ ወን የኖቤል ተሸላሚ ሆነ ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-11-08