ሀገሬ ቲቪ

በትግራይ ከተሞች የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ተባለ

የፌደራል መንግሥት እና ህወሓት የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ በምግብ ፍጆታዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ታይቷል ተባለ ።

በመቀሌ እንዲሁም በአንዳንድ የትግራይ ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቦ የነበረው የጤፍ እና ሌሎች የምግብ ፍጆታዎች ዋጋ ድንገተኛ ቅናሽ ማሳየቱን ቢቢሲ ከቦታው አረጋግጫለሁ ሲል ዘግቧል ።

አንድ ኩንታል ጤፍ ከ14ሺህ ወደ 8ሺህ እንዲሁም አንድ ኩንታል ስንዴ ከ9ሺህ ወደ 3ሺህ ብር ወርዷል ተብሏል ። በተመሳሳይ የዘይት፣ የስኳር እና የበርበሬ ዋጋም መጠነኛ ቅናሽ እንደታየበት የመቀለ ነዋሪዎች ገልጸዋል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-11-09