ሀገሬ ቲቪ

ለሳምንታት ተቋርጦ የቆየው በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ሥራ ኅዳር 12 ይጀመራል

ለሳምንታት ተቋርጦ የቆየው በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ሥራ ኅዳር 12 እንደሚጀመር ብሄራዊ አስመላሽ ኮሚቴው አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳስታወቀው ተመላሾች የሚያርፉባቸው መጠለያዎች ብሄራዊ ኮሚቴው አዘጋጅቷል ።

ብሄራዊ ኮሚቴው ከአሁን ቀደም ባስተባበራቸው የአውሮፕላን በረራዎች 71 ሺህ 697 ፍልሰተኞች ወደ አገራቸው የመለሰ ሲሆን፣ በቀጣዩ ዙር ለመመለስ የታቀደው የመጨረሻዎቹን 30 ሺህ 303 ፍልሰተኞች ነው።

በብሩክ ያሬድ
2022-11-09