ሀገሬ ቲቪ

ዩጋንዳ በኢቦላ ምክንያት ትምህርት ቤቶችን ዘጋች

በዩጋንዳ ስምንት ህፃናት በኢቦላ ምክንያት መሞታቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንዲዝጉ ተወሰነ።

በዩጋንዳ እንደገና በተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ በዚህ ወር መጨረሻ ብቻ ህፃናትን ጨምሮ 23 ተማሪዎች እስካሁን እንደተጠቁ ተገልጿል።

በዋና ከተማዋ በካምፓላ በሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የወረርሽኙ ዋና ማዕከል በሆነችው በአጎራባችዋ ዋኪሶ አውራጃና ሙቤንዴ ውስጥ ውረርሽኙ መከሰቱን የሃገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር ጃኔት ሙሴቬኒ መግለፃቸውን ኢስት አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።

በብሩክ ያሬድ
2022-11-09