
የአለም ገንዘብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክርስቲና ጆርጂዮቫ የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ በታዳሽ ሃይል ልማት ቢሰማራ ውጤታማ እንደሚሆን ገለጹ።
ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለው ኢኮኖሚ ላይ መዋዕለ-ነዋይን ማፍሰስ ከተቻለ በርካታ የስራ እድል መፍጠር እንደሚቻልም ዋና ዳይሪክተሯ በግብፅ ሻርም አል ሼክ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት 27ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ባደርጉት ንግግር ገልፀዋል።
በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እንደ ድርቅ፣ ጎርፍና የባሕር ዳርቻዎች መሸርሸር ባሉ የአየር ንብረት ለውጥ ክስተቶች እየተጎዳች ባለችው አፍሪካ ታላላቅ አለም አቀፍ ኢንቨስተሮች በታድሽ ኃይል ዘርፍ መዋለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ እነርሱም ተጠቅመው የለውጡን ተጽኖም ይቀንሳሉ ብለዋል።
አፍሪካ የአየር ጸባይ ለውጥ ተጽኖን የምትቋቋመው በእንዲህ አይነት መንገድ ነው ማለታቸውንም ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
በብሩክ ያሬድ
2022-11-09