ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች ፍላጎቶችን ለማሟላት ምርቶችን ከውጭ ጭምር ታስገባለች ።
በዘፉ ላይ ጥናት ያደረጉት ባለሞያዎች ደግሞ ሀገራችን ከምታመርታቸው የግብርና ምርቶች ቀላል የማይባል መጠን ምርት በየዐመቱ ለብልሽት እና ለብከነት እንደሚጋለጡ ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን የግብርና ምርቶች መጓጓዣና ማከማቻ ስርዐትን ለማሻሻል ግብርና ሚኒስተርን ጨምሮ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር የምክክር አውደ ጥናት አኪያሒዷል።
በመድረኩ የድህረ ምርት አያያዝን በተመለከተ ያደረጉትን ጥናት ያቀረቡት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምርት ባለሞያ ፕሮፌሰር አሊ መሀመድ በኢትዮጵያ በየዐመቱ በሚባክነውና በሚበላሸው ምርት ሳቢያ ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርጋለች ብለዋል ።
ይህ ችግር በሌሎች ሀገራትንም ይፈትን እንደነበርና በወሰዱት ፈጣን እርምጃ በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀነሱት የሚናገሩት ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ምርቶች ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ አለባት ብለዋል ።
ይህንን ሀገራዊ ችግር ለመቅረፍ ከመንግስት በተጨማሪ የግል ባለሀብቶችም መሳተፍ እንዳለባቸው በ አውደ ጥናቱ ተጠቁሟል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-11-11
