በበጎ ፍቃደኞች የሚሰጡ ህከምናዎች የሆስፒታሉን ጫና እያቃለ ሉ እንደሆነ የየካቲት 12 አጠቃላይ ሆስፒታል ገለፀ። አብዛኞቹ በጎ ፍቃደኞች ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ስለሆነ ለእውቀት ሽግግርም ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተነግሯል ።
ጉሮሮ እና በጆሮ ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች በሃገር ውስጥ ህክምና ለመስጥት አስቸጋሪ ስለነበሩ አቅም ያላቸው ሰዎች ከአገር ውጭ ወጥተው ለመታከም ይገደዱ ነበር።
አሁን ግን ከስዊድን በሚመጡ በጎ ፈቃደኛ ሃኪሞች በአመት ሁለት ጊዜ ህክምናው እየተሰጠ ይገኛል። እስካሁንም 200 የሚሆኑ ሰዎች ህክምናውን አግኝተዋል።
መቀመጫውን በሲዊዲን ያደርገውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኢንት ፕላስ የተሰኘው ድርጅት በርካታ በጎፍቃደኞችን በማሰተባበር በዓመት ሁለት ጊዜ በጥቁር አንበሳና በየካቲት 12 ሆሰፒታል በመገኘተ ህክምና እየሰጡ ይገኛሉ ።
በሰዊዲ ኡሳላ ዪኒቨርስቲ ስፔሻል ነርስ የሆኑት ዘውዱ መላኩ ENT+ የተሰኘውና የከአንገት በላይ ህክምና በጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎችን ቡድን ዋነኛ አባል እንደንገሩን ቡድኑ ህክምና መሰጠት ብቻ ሳይሆን ዕውቀትም ያሻግራሉ ።
በየካቲት 12 ሆስፒታል ከአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ካሳየ አሽሊ ከስዊዲን የሚመጡት የህክምና ባለሙያዎች ሁሌም ለኛ እፎይታን እንደሰጡን ነው ብለዋል።
እንደ ENT+ ሁሉ በውጭ ሀገር የሚኖር ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን በእንደዚህ አይነቱ በጎ ፍቃድ ቢሰማሩ የብዙዎችን ጤና መመልስ እንደሚችሉ ይታመናል።
በማህሌት አማረ
2022-11-11
