ሃገራት ለሰላምዊ ጥቅም እናለማለን በለው የሚጀምሩት የኒውክሌር ሃይል ከግዜ ወደ ጊዜ ወደ ወታደራዊ ገብአትነት እየተቀየረ መጥቷል።
አለም በአየር ንበረት ለውጥ ሳቢያ ሰጋት ወስጥ በገባበት በዚ ወቅት ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የኢራን የኒውከሌር ፕሮግራም አሰሰቦኛል በሏል።
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የኢራን የኑክሌር ፕሮግራም አስተማማኝ አይደለም ያለ ሲሆን የቴራን ባለ ሥልጣናት የኑክሌር ጣቢያዎች እንዳይገቡም ጠይቋል ።
የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ ኢራን ከፍተኛ መጠን ያለው ዩራኒየምን ክምችት እንዳላት አውቃለሁ ብልዋል ። የድርጅቱ ባለሥልጣናት በኅዳር ወር መጨርሻ ላይ ቴራንን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ።
የተባበሩት መንግሥታት የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ድርጅትም ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት ላይ “አሁን ያለው ሁኔታ ረዘም ላለ ጊዜ በቆየ መጠን ሰጋትነቱ የዚያኑ ያህል ይጨምራል” ብሏል።
አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በሦስት ቦታዎች የተገኙ ያልታወቁ የዩራኒየም ቅንጣቶች አመጣጥን አስመለከቶ ከቴህራን ማብራሪያ እንዲሰጠው እየጠበቀ ነው ።
ኢራን በበኩሏ (IAEA) አይ ኤ ኤ በጉዳዩ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ እንዲያቆም ብትጠይቅም ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግን ለሁሉም የኑክሌር እንቅሰሳሴ መልስ መስጠት እንደሚያስፈልገው ይናገራል።
የአለም አቀፉ አቶሚክ ተቆጣሪ ሃላፊ ራፋኤል ግሮስሲ ግልጽ እና ያልተጠበቁ አደጋዎችን በመከላከሉ ረገድ ምንም ለውጦች አለመኖራቸው እጅግ በጣም ያሳስበናል ብለዋል ። አይ ኤ ኤ ሐሙስ ባወጣው ሌላ ሪፖርት ላይ የኢራን የበለጸገ ዩራኒየም ክምችት በ267.2 ኪሎ ግራም እንደቀነሰ ገልጿል ።
ለጦር መሣሪያ ከሚፈለገው 90% ገደማ የሚሆነው የዩራኒየም ክምችት በአሁኑ ጊዜ 62.3 ኪሎ ግራም ሲሆን ባለሙያዎች እንደሚሉት ግን 50 ኪሎ ግራም የኑክሌር ቦምብ ለመሥራት በቂ ነው። ሆነም ቀረ ኢራን አሁንም የኒወክሊር ቦንቦችን መስራት የሚያስችል አቅሟ አሁንም አልቅነሰም።
ኢራን ከሃያላኑ መንስግስታት ጋር በ2015 የኒወክሌር ፕሮግራምን ለመግታት ሰምምነትን ብትፈጸምም ከሶስት አመታት በኋላ አሜሪካ ሰምምነቱን አፍርሳለች።
ይህ በአንዲህ እንዳለ ኢራን ሀይፐር ሶኒክ ባሊስቲክ ሚሳይል መገንባቷን የገለጸች ሲሆን ሚሳኤሉ በኢራን ጦር ሀይል እንደተሰራ ተገልጿል፡፡ከድምጽ አምስት እጥፍ ፍጥነት እንዳለው የተገለጸው ይህ ሀየፐር ሶኒክ ሚሳኤ በአይን ለመለየት እንደማይቻል ነው የተገልጸው ፡፡
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-11
