ሀገሬ ቲቪ

የትምህርት ሚኒስቴር ለፈጠራ ባለሙያዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ

የትምህርት ሚኒስቴር ለፈጠራ ባለሙያዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ያለው ሲካሄድ የቆየው አገር አቀፍ የሳይንስ ቀን ማጠናቀቂያ የመምህር እና ተማሪዎች የፈጠራ ስራ ውድድር ላይ ነው።

የአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፋንታ ማንደፍሮ በማጠቃለያ ንግግራቸው ሳይንስ አውቀነው የመንቀመጥበት ሳይሆን የዕለት ተዕለት ኑሯችንን የምናቀልበት ነው ብለዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው የሀገር እና ማህበረሰብ ችግሮቻችንን ለመቅረፍ በፈጠራ ስራዎች ላይ ጠንክረን መስራት እንደሚገባን ጠቁመዋል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-11