ሀገሬ ቲቪ

ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጽያ በሰሜኑ ጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች ደጋፍ አደረገ

በሰሜኑ ጦርነት እና በተለያዩ አካባቢዎች በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለው በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጽያ ከዩኒሴፍ ጋር ባገኘው የውኃና የንጽኅና አገልግሎት መስጫ ተቊማትን ገንብቶ ዛሬ አስረክቧል።

ፕሮጀክቱ 70 ሚሊየን ብር ፈጅቷል።አጣዬ እና ደብረብርሁን እና ሸዋሮቢት እነዚህ ተቊማት የተገነቡባቸው ከተማዎች ናቸው በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 167ሺህ ዜጎች ተጠቃሚ መኾናቸውን የፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጽያ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ወንደሰን ዓለሙ ተናግረዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-11