በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ ተገለጸ።
የዕጣ መርሃ ግብሩን አስመልክተው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
ለዚህ ዕጣም 146ሺ 892 ቆጣቢዎች በዕጣው መካተታቸው ተገልጿል። በመግለጫው በነገው ዕለት በሁለቱም የቤቶች መርሃ ግብር 25 ሺ 791 ቤቶች ዕጣ የሚወጣባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
በሁለቱም መርሃ ግብሮች በዕጣው የተካተቱ ቆጣቢዎች እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 በአግባቡ የቆጠቡ መሆናቸው ተመላክቷል። በዕጣ ለሚተላለፉ ቤቶችና ለመሠረተ ልማት ግንባታ 21 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉም ተገልጿል።
በብሩክ ያሬድ
2022-11-14
