ሀገሬ ቲቪ

ሳፋሪኮም በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከሰባት መቶ ሺ በላይ ደንበኞች እንዳገኘ ገለፀ

ሳፋሪኮም በኢትዮጲያ የቴሌኮም ገበያውንን በተቀላቀለ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከሰባት መቶ ሺ በላይ ደንበኞች ማግኘቱን ገለጸ።

የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ፔቴር ኔዴግዋ በየቀኑ እስከ ሃያ ሺ የሚደርሱ ሰዎች የሳፋሪኮም ደንበኛ እየሆኑ ነው ብለዋል። ሳፋሪኮም በኢትዮጲያ እስካሁን በአስራ አንድ ከተሞች በ 2G፣ 3G እና 4G የኔት ዎርክ አገልገሎት እየሰጠ ነው።

በፈረንጆቹ 2023 አገልግሎቱን ወደ ሃያ አምስት ከተሞች በማሳደግ የሃገሪቱን ሃያ አምስት በመቶ ህዝብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አፍሪካን ቴክ ዘግቧል።

በማህሌት አማረ
2022-11-14