
አፍሪካዊቷ ሞዛምቢክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አውሮፓ የተፈጥሮ ነዳጅ ላከች። ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ኒዩሲ ታሪካዊ ያሉትን የተፈጥሮ የነዳጅ ምርት በእንግሊዝ የነዳጅ ጫኝ መርከብ አማካኝነት ወድ አውሮፓ መላካቸውን አስታውቀዋል።
አውሮፓዊያን በሩሲያ ላይ ጥገኛ የሆኑበትን ነዳጅ አማራጭ ሲፈልጉ በነበረበት ሰአት ሞዛምቢክ ጋዝ ማግኘታቸው ሩሲያ በነዳጅ መርቷ ላይ ያላትን ትምክህት ይቀንስላቸዋል ተብሏል።
ነገር ግን ከሞዛምቢክ ወደ አውሮፓ የተላከው የነዳጅ ምርት መዳረሻው እንዳልታወቀ ቢቢሲ ዘግቧል።ሞዛምቢክ የናዳጅ ምርቷን ወደ አውሮፓ መላክ መጀመሯ ለኢኮኖሚዋ መነቃቃት እንደሚፈጥርላትም ተገልጿል።
በማህሌት አማረ
2022-11-14